ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ሀገር ናት።

7

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

በሴኔጋል ዳከር የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር በዓለም የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ 1ኛ ሆነን በማጠናቀቃችን እንኳን ደስ አለን!

‎ሀገራችን በዳካር በተካሄደው የ2026 የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች እንቁ ልጆቻችን በአትሌቲክስ ውድድር 5 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ለሀገር ድል አብስረዋል። ወጣቶቻችን ኢትዮጵያ በእናንተ ኮርታለች።

በስፖርቱ ዘርፍ ታዳጊዎች ላይ በርትተን ከሠራን በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ መድረኮች ወደ ቀደም ክብርና ከፍታችን የምንመለስበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይህ ስኬት አመላካች ነው፡፡

የመደመር መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል በመፈጸም፤ የስፖርት መሰረተ ልማት ማስፋፊያዎችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየገነባ ይገኛል።

ይህም በስፖርት የዳበረ፣ ብቁ፣ አምራች እና ውጤታማ ዜጋን በመፍጠር በዓለም አቀፍ መድረኮች ያለንን የአሸናፊነት ክብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግር፤ ስማችንን ከፍ የሚያደርጉ አትሌቶችን በማፍራት ውጤታማነታችንን ይበልጥ የሚያልቅ ትልቅ ማሳያ ነው ።

በዳካር ኦሎምፒክ ደማቅ ውጤት እንዲገኝ ሚናችሁን ለተወጣችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናዬን እያቀረብሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_03_2019_ዓ_ም
‎
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous article‎🇪🇹የምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ለሰው ልጆች ህልውና የዛሬው አርአያነት!