‎የምሥቅ አፍሪካ ቀጣናን በማይበጠስ የልማት እና የሰላም ገመድ እያስተሳሰረች ያለችው ኢትዮጵያ!

11

‎ቀጣናዊ ሰላም፣ የጋራ ልማት እና የዲፕሎማሲ ማዕቀፎች የነባራዊው ዓለም አደረጃጀት መሠረታዊ መርሆዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ትስስር እንዲጎለብት፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና ሰላማዊ አብሮ መኖር እንዲረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የታሪክ፣ የጂኦ-ፖለቲካ እና የጋራ ብልጽግ ፖሊሲ መሠረት ያለው ነው።
‎
‎ኢትዮጵያ በቀጣናው የልማት አጋርነትን በመገንባት፣ የኢኮኖሚ እና የኀይል ትስስርን በማስፋት እንዲሁም “የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፍትሔ” በሚለው መርህ ላይ ጸንታ በመቆም ለሰላማዊ አብሮ መኖር ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች።
‎
‎በተቃራኒው የቀጣናውን ተፈጥሯዊ ትስስር ለማሰናከል፣ የታሪካዊ ወዳጅነቶችን ገመድ ለመበጠስ እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎቶቻቸውን ለመጫን የሚጥሩ የውጭ ኀይሎች እና ወኪሎቻቸው የሚያካሂዱት የትንኮሳ እና የሴራ ፖለቲካ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፋይዳ ቢስነቱ እየጎላ መጥቷል።
‎
‎ኢትዮጵያ በቀጣናው የምትከተለው የውጭ ጉዳይ እና የዲፕሎማሲ ፖሊሲ በጋራ እድገት እና ደኅንነት ላይ የተመሠረተ ነው።
‎
‎ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ እና በሌሎች የታዳሽ ኀይል ማመንጫዎቿ አማካይነት ለጎረቤት ሀገራት (ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ) የኤሌክትሪክ ኀይል በማቅረብ የቀጣናው የኢኮኖሚ አምድ ኾናለች።
‎
‎አሸባሪነትን፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን በጋራ ለመከላከል ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር እና በባለቤትነት መንፈስ መሥራት የፖሊሲዋ መሠረት ነው።
‎
‎የሀገራትን ድንበር የጋራ ንግድ፣ የባሕል ልውውጥ እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማዕከል በማድረግ ግጭቶችን ማስወገድ እና ዘላቂ ሰላምን መገንባት ላይ አተኩራም እየሠራች ነው።
‎
‎የአፍሪካ ቀንድን ስትራቴጂካዊ ቦታ ለመቆጣጠር በሚደረግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ፉክክር ውስጥ የውጭ ኀይሎች በሀገራት መካከል አለመተማመንን ለመፍጠር፣ የውስጥ ግጭቶችን እና የኢኮኖሚ ጫናዎችን ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረቶች አጥብቃ ትቃወማለች።
‎
‎የኢትዮጵያ እና የጎረቤት ሀገራት ሕዝቦች ግንኙነት በጊዜያዊ የፖለቲካ ውጥረት ወይም በውጭ ኀይሎች ሴራ የሚናጋ ሳይኾን በጽኑ ታሪካዊ እና ማኅበራዊ ትስስር የተሰናሰለ ነው።
‎
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት “ቀጣናዊ ትስስር የጋራ ህልማችንን እውን ለማድረግ እና የሕዝቦቻችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ እጅግ ጠቃሚ እና አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።

ኢትዮጵያ የምታካሂዳቸው የልማት ሥራዎች የታላቁ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች የኀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለራሷ ብቻ ሳይኾን ለጎረቤቶቿም የጋራ እድገት የተዘጋጁ ናቸው”
‎
‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የአፍሪካ ቀንድ ሰላም የሚረጋገጠው በራሳችን አቅም እና በውይይት እንጂ የውጭ ኀይሎችን አጀንዳ በመሸከም አይደለም፤ ኢትዮጵያ የትኛውንም ሀገር የማጥቃት ወይም የሀገራትን ሉዓላዊነት የመዳፈር ፍላጎት የላትም፤ ነገር ግን የሀገሯን ሉዓላዊነት እና የሕዝቦቿን ጥቅሞች በጽናት ትጠብቃለች።

የውጭ ኀይሎች በቀጣናው ክፍተት ለመፍጠር የሚያደርጉት ሙከራ የጋራ ትስስራችንን ከመፈተን ባለፈ ዘላቂ ውጤት አያመጣም፤ ምክንያቱም የእኛ ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ ነው” ብለዋል።
‎
‎የውጭ ኀይሎች ትንኮሳ እና ጣልቃ ገብነት ጊዜያዊ ውጥረቶችን ሊፈጥር ቢችልም በኢትዮጵያ መሪነት እየተገነባ ያለው የቀጣናዊ ትስስር፣ የጋራ ኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ማዕቀፍ ግን የረጅም ጊዜ መረጋጋት እና ብልጽግና መሠረት ስለመኾኑም ነው የጠቆሙት።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_03_2019_ዓ_ም
‎
‎ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleኢትዮጵያ የተሳካ COP32 ለማካሄድ ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት አላት።
Next article‎🇪🇹 የኅብረተሰቡን እንግልት ያስቀረው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት!