ከምድር እስከ ሰማይ፤ ከባሕር እስከ ሳይበር የነገሠው የኢትዮጵያ አለኝታ!

4

የጽናት እና የኩራት መገለጫ ነው። እንደ ወርቅ ተፈትኖ፣ እንደ ብረት ጠንክሮ፣ በአለት ላይ ሠንደቋን በጽናት ተክሏል። የማይናወጥ ጀግንነቱን ከሀገሩ አልፎ በአፍሪካ ቀጣና በሰላም አሥከባሪነት በመሠማራት አረጋግጧል።

ክንደ ብርቱው የሀገር የመከላከያ ሠራዊት በየጊዜው ራሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ የላቀ የቴክኖሎጂ በመታጠቅ ግዙፍነቱን ገንብቷል። የመከላከል እና የማጥቃት አቅሙን አይደፈሬ አድርጓል።

በወታደራዊ ሳይንስ እና በጥበብ ጎልብቷል። ሀገርን ከማይናወጥ የሰላም ማማ ላይ ለማስቀመጥ በቁርጠኝነት ይተጋል።

በእሳት የተፈተነ፣ የዘመነ ቴክኖሎጂን የታጠቀ፣ ከምድር እስከ አየር፣ ከባሕር እስከ ሳይበር ለኢትዮጵያ ክብር በጽናት የቆመ ነው። የጦር ቴክኖሎጂን በራስ አቅም ማምረት እና ማሻሻል ላይ በትኩረት ሠርቷል።

በፈታኝ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እና አየር ንብረት አልፎ የጠላትን ምሽግ ይጥሳል፣ የኢትዮጵያን ጠላቶችን ቅስም ይሰብራል፣ የውስጥ ባንዳዎችን በመሥበር የሉዓላዊነት ምሽግ ኾኗል።

በተቋሙ የተደረገው ሪፎርም ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስቀድም፣ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ፣ ብሔራዊ ክብሯን የሚያስጠብቅ ኾኗል። የኮማንዶ እና አየር ወለድ ክፍሎቹን ፍጥነት እና ጥራት አሥተማማኝ ለማድረግ ተሠርቷል።

አይበገሬው አየር ኀይል በድሮኖች፣ በዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች፣ በተወንጫፊ ጀቶች የኢትዮጵያን የአየር ክልል 24 ስዓት በንቃት ይጠብቃል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ጠላቶች እሳቤ እና ፍላጎት በላይ ኾኗል። ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ይበልጥ በመታጠቅ ታሪካዊ ጠላቶቿ ላይ ድንጋጤን ፈጥሯል። የግብጽ እና የሻዕቢያ መንግሥት ተላላኪ የውስጥ ባንዳዎችን ምኞት በማምከን ታሪካዊ ሤራዎችን አክሽፏል።

በዚህም ታሪካዊ ጠላቶቿ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የመፈጸም አቅም እንዲያውቁ፣ የማይናወጥ ጀግንነቱን እንዲመለከቱ፣ የቀጣናው የሰላም ዋስትና መኾኑን እንዲገነዘቡ አድርጓቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ሠራዊት የአፍሪካ ሀገራት በሚገጥማቸው ችግር ውስጥ ድንበር ተሻግሮ ሰላምን ለማስከበር የሚያስችል ብቃት ያለው አሥተማማኝ ሠራዊት ነው። የእኛ ዓላማ ውጊያ የሚያስቀር፣ የሚጨርስ ጠንካራ ኀይል መገንባት ነው ብለዋል።

የሠራዊቱ ተልዕኮ ኢትዮጵያን መገንባት፣ መጠበቅ፣ ማጽናት እና ማሸጋገር መኾኑንም ተናግረዋል። ከአየር ጥቃት ኢትዮጵያን መከላከል የሚችሉ በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለመታጠቅ እና ብቃትን ለማሳደግ ተሠርቷል ነው ያሉት።

የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለመገንባትም ይሠራል። በቀጣናው የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ኢትዮጵያ ትገነባለች ብለዋል።

በቂ ዝግጅት ያላቸው ሀገራት በቀላሉ አይደፈሩም ነው ያሉት። ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው የጦር ቴክኖሎጂዎች ለቀጣናው ሰላም ዋስትና መኾናቸውንም ተናግረዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_02_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ ጋር ተወያዩ።
Next article🌾 በአማራ ክልል ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል።