
በአማራ ክልል የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እና መሰል ችግሮች እንዳይበላሹ እና የድኅረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ በኮምባይነር የታገዘ ተግባር እየተከናወነ ነው።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የክልሉ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ምርት እንዳይባክን ዘመናዊ መሣሪያዎች ላይ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በምሥራቅ እና በምዕራብ ጎጃም፣ በምዕራብ ጎንደር እና በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች የስንዴ ምርትን በፍጥነት እና በጥራት ለመሠብሠብ ከ80 በላይ ኮምባይነሮች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።
አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በተሻለ ቅንጅት እና ቅልጥፍና እንዲሠበሥቡም አሳስበዋል።
በተያያዘ መረጃ በዘንድሮው ዓመት ከ734 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ በማልማት ከ95 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
