
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) ከCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ የድርድር ቡድን (AGN) ሊቀመንበር አንትዊ–ቦአሲያኮ አሞአ ( ዶ.ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱ ለአፍሪካ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ፍትሐዊ ሽግግር እና ትግበራ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ታዳጊ ሀገራት በብሔራዊ የተወሰኑ አስተዋጽኦዎቻቸው (NDCs) እና በብሔራዊ የማጣጣሚያ ዕቅዶቻቸው (NAPs) ትግበራ የበለጠ ድጋፍ እንዲያገኙ፣ የአየር ንብረት እርምጃዎች የአፍሪካን የልማት ቅድሚያዎች እንዲመልሱ አስፈላጊነቱን ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለCOP32 ዝግጅቶች እየተጠናከሩ በሚሄዱበት ወቅት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የድርድር ቡድን ጋር የቅርብ ምክክር እንደምታደርግ አረጋግጠዋል። በአንታልያ የተሳካ ውጤት ማስመዝገብ፣ በድርድሩ ሂደቱ ላይ ያለውን እምነት ማጠናከር እና ከቃል ኪዳኖች ወደ ተግባራዊ አፈጻጸም መሸጋገር አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቅድሚያዎች እና አመለካከቶችን (Africa’s priorities and perspectives) ወደ COP32 በሚደረጉ ዝግጅቶችና ውይይቶች ሂደት በጥንካሬ እንዲንጸባረቁ ከአፍሪካ የድርድር ቡድን ጋር በቅርበት መሥራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።
#COP31 #COP32 #AfricaForClimate
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
