🔥 የእግር እሳቱ ቁጭት፡- የኢትዮጵያ የባሕር በር የሕልውና ትግል 🇪🇹

5

 

በ”ይነዳል ይቆጫል እንደ እግር እሳት፣
ወደ ፊት ሲሄዱ ከኋላ መቅረት፤”

ይህን ስነ ቃል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ ሲናገሩት ተደምጠዋል። ዓለም በፈጣን ዕድገት ውስጥ ባለችበት በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ በጂኦግራፊያዊ እስር ቤት ተወስና እና በውስጣዊ ክህደት ታጥራ መቅረቷን በጉልህ ይገልጻል።

የዘመኑን የሥልጣኔ ፉክክር መቀላቀል ሲገባ በባንዳዎች ርካሽ ሴራ ከኋላ መቅረት የቆመ እሳት ኾኖ የሚነድ እና የሚቆጨው የትውልድ የሕልውና አጀንዳ መኾኑንም ይኸው ሃሳብ ያሳያል።

ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ታላቅ ሀገር ከቀይ ባሕር በቅርብ ርቀት ላይ እያለች ወደብ አልባ ኾና መታፈኗ ለዜጎችም ኾነ ለሀገር መሪዎች እረፍት የሚነሳ የዘመን ቁስል ነው። ይህ የኢኮኖሚ ጡንቻን ያዳከመ፣ ከፍተኛ የሎጀስቲክስ ወጪ እንዲባክን ያደረገ እና ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎን የገደበ ታሪካዊ ግፍ ሊያስቆጭ እና ሊያንገበግብ ይገባል።

የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት እና ከጂኦግራፊያዊ እስር ቤት መላቀቅ እንደ ስጋት የሚመለከቱት ግብጽ እና ኤርትራ ሀገሪቱ በድህነት አዙሪት ውስጥ እንድትቀጥል ይፈልጋሉ።

ይሁን እንጂ ከውጭ ጠላቶች ሴራ በላይ አሳዛኙ እና ቁጭቱን ድርብ የሚያደርገው በራሷ የኢትዮጵያ ማኅጸን የተፈጠሩ ኃይሎች የጥፋት አሥፈጻሚ መኾናቸው ነው። ሀገራቸው ከድህነት ወጥታ የባሕር በር ባለቤት እንድትኾን ከመታገል ይልቅ በጠላቶች አጀንዳ ተመድበው የሀገራቸውን የሥልጣኔ ጉዞ ከኋላ ይጎትታሉ። የባሕር በር ጥያቄን ከማገዝ ይልቅ በተቃራኒው መሰለፋቸው ከባድ ታሪካዊ ክህደት እና የትውልድ ጠላትነት ነው።

ዓለም የጋራ ብልጽግናን ሲያስብ እነሱ የውጭ ጠላት ኪራይ ሰብሳቢ በመኾን የገዛ ሀገራቸውን በር ለመዝጋት ይዋጋሉ። ግብጽ እና ኤርትራ ኢትዮጵያን በውክልና ጦርነት ለማዳከም የዘረጉትን ወጥመድ በደስታ ተቀብለው ሀገርን ማተራመሳቸው “…ወደፊት ሲሄዱ ከኋላ መቅረት” ለሚለው መሪር እውነት ዋነኛ ተዋንያን አድርጓቸዋል።

ዓለም ቆሞ አይጠብቅም፤ የጊዜ ባቡርም አያዘገይም። ይህን መሪር እውነት ተረድቶ ከንቱ የኾኑ የውስጥ መከፋፈሎችን ወደ ጎን በመተው እና በአንድነት በመነሳት የባሕር በር አልባነትን ፈተና ወደ ልማት ማቀጣጠያ ሞተርነት በመቀየር ሉዓላዊነትን ማስከበር የትውልዱ ታሪካዊ አደራ ነው።

#Ameco #RedSeaAccess ​#EthiopiaRising

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_30_2019_ዓ_ም

✍️ በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ግጭት ይብቃ፤ ሰላም ይንገሥ🇪🇹
Next articleበCOP31 የኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ተከፈተ። 🇪🇹