የኢትዮጵያን የኢነርጂ ታሪክ የሚቀይረው የኒውክሊዬር ፕሮጀክት!

8

ሀገራት የኀይል አቅርቦታቸውን አሥተማማኝ ለማድረግ ከውኃ፣ ከፀሐይ፣ ከነፋስ ኀይሎችን ያመነጫሉ።ሰላማዊ የኒውክሊዬር ኀይልን በመጠቀም የኀይል አቅርቦታቸውን የሚያሟሉም ሀገራት አሉ።ሰላማዊ የኒውክሊዬር ኀይል ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና

የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው። የኢትዮጵያ የጉባ ብሥራት የኾነው ሰላማዊየኒውክሊዬር ኀይል ግንባታ ደግሞ የበርካታ ሀገራትን ቀልብ ቆንጥጦ ይዟል።ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ለመገንባት ወደ ሥራ መግባቷም

ብዙዎችን አስደንቋል። አፍሪካዊያን በራሳቸው አቅም ማደግ እንደሚችሉም ያሳየ ጅማሮ ነው። የኢትዮጵያ የኒውክሊዬር ኀይል ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሽፈራው ተሊላ ኢትዮጵያ በቀጣይ ልታሳካ የምትፈልገውን ራዕይ እውን ለማድረግ ኢነርጂ ወሳኝ ነው ብለዋል።ኢነርጂ የኢኮኖሚ ዋና

አንቀሳቃሽ ኀይል ነው። ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪያላይዜሽን ሽግግር ላይ መኾኗ፣ የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኀይል አቅርቦት የሚፈልጉ በመኾናቸው ፊቷን ወደ ሰላማዊ የኒውክሊዬር ኀይል ምርት እንድታዞር አድርጓታል ነው ያሉት። የኒውክሊዬር ኀይል

ለረጅም ጊዜ ኀይልን ማመንጨት የሚችል እና የኀይል መቋረጥ ችግርን የሚቀርፍ መኾኑ ተመራጭ ያደርገዋል ነው ያሉት። ከፍተኛ የኢነርጂ ክምችትን የሚይዝ እና የኀይል አቅርቦትን የሚፈጥር መኾኑንም ተናግረዋል።ኮሚሽኑ በተቋቋመ በአንድ ዓመት ውስጥ የሰው ኀይልን የማሟላት፣

ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጅ ተቋም ጋር ቅንጅት የመፍጠር፣ የቦታ ልየታ እና ጥናት፣ የቅድመ ግንባታ ዝግጅት፣ የቴክኒክ እና ሌሎች ሥራዎችን መፈጸሙን ገልጸዋል።ብቁ ባለሙያን በማፍራት ብሔራዊ አቅምን ለመፍጠር እየተሠራ ነው ብለዋል። ሰላማዊ የኒውክሊዬር ኀይል

ግንባታው ሲጠናቀቅ በሁለት ዩኒቶች 2 ሺህ 400 ሜጋ ዋት ኀይል የሚያመነጭ መኾኑን ያነሱት ምክትል ኮሚሽነሩ ከሕዳሴ ግድብ የሚበልጥ ኢነርጂን ያመነጫል ነው ያሉት።የኒውክሊዬር ኀይሉ ለካንሠር ሕክምና፣ ለግብርና ምርታማነት መጨመር፣ በግብርናው ዘርፍ የሚከሰቱ

በሽታዎችን ለማከም፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለውኃ ልማት እና ለሌሎች ዘርፎችም ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ይበልጥ እንድታጠናክር፣ የኀይል አቅርቦቷ አስተማማኝ እንዲኾን፣ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነቷ እና ዕድገቷ እንዲጠናከር፣ ሕዝቦቿ በቂ የኀይል አቅርቦት

እንዲያገኙ ያስችላል ነው ያሉት።በቀጣይ የትምህርት ተቋማት የኒውክሊዬር ቴክኖሎጂን ያካተተ የትምህርት ፍኖተ ካርታ እንዲተገብሩ በቅንጅት ይሠራል ነው ያሉት። ለዜጎች ዘርፈ ብዙ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም አንስተዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_30_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበአማራ ክልል የማዕድን ላብራቶሪ ሊገነባ ነው።
Next article“ግጭት ይብቃ፤ ሰላም ይንገሥ🇪🇹