የአማራ ክልልን የማዕድን ሀብት በምርምር ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

8

 

የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የሥነ ምድር ካርታ ሥራ፣ ማዕድን ፍለጋ እና ክምችት የጂኦ ሳይንስ ጥናት ለማካሄድ በክልሉ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ጋር የውል ሥምምነት ተፈራርሟል።

የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ ኀላፊ ኃይሌ አበበ በክልሉ ለሀገር ዕድገት ከፍተኛ ሚና የሚወጡ የተለያዩ የማዕድን ሃብቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

የማዕድን ዘርፉን በዘመናዊነት መምራት፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ በዘላቂነት ማልማት እና ከዘርፉ የሚገኝን ጥቅም ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት።

የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማረጋገጥ የሚቻለው በዕውቀት እና በምርምር የተደገፈ አሠራር መከትል ሲቻል መኾኑን የክልሉ መንግሥት በጽኑ ያምናል፤ ለዚህም ነው የውል ሥምምነቱ ያስፈለገው ብለዋል። ለሕዝብ ተጠቃሚነት በጋራ እንሠራለን ነው ያሉት።

📌 ኀላፊው ከሥምምነቱ ምን ይጠበቃል አሉ?

👉የማዕድን ሃብት ጥናትን ይበልጥ በማጠናከር በመደርደሪያ ከማስቀመጥ አልፎ በተግባር ችግር ፈች እንዲኾን መሥራት ይገባል ብለዋል።

👉የቤተ ሙከራ አቅምን ያገናዘበ የማዕድን ዓይነት፣ መጠን፣ ጥራት እና ክምችን በመለየት በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራን ማከናወን ያስፈልጋል ነው ያሉት።

👉 ጥናቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለኢንቨስትመንት እንዲውሉ ማስቻል፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት ይገባል ብለዋል። በዘርፉ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

ዓለም በቴክኖሎጂ እና በማዕድን ሃብት እየተቀየረ በመኾኑ የክልሉን የማዕድን ሃብት በማልማት የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት እና የክልሉን የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በሥምምነቱ ላይ የተገኙት በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ጀጃው ደማሙ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲዎች ባለፉት ዓመታት

ከማዕድን ቢሮ ጋር በቅርበት እየሠሩ ቆይተዋል ብለዋል። የክልሉ የኢኮኖሚ መውጫ መንገድ የኾነውን የማዕድን ሃብት ለማልማት እና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ተቋማቱ በጋራ ይሠራሉ ነው ያሉት።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_28_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ከቀጣይ ጥር ወር ጀምሮ ስምንት የክልሉ ተቋማት ወደ ሪፎርም ትግበራ ይገባሉ”
Next article🌾 ዘመናዊ ግብርና ለምግብ ሉዓላዊነት