
የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በመጀመሪያው ዙር ወደ መንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም የሚገቡ የክልል ተቋማትን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አፈጻጸም ገምግሟል።
የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ባንቺአምላክ ገብረማርያም ሪፎርሙ በዝግጅት፣ በትግበራ እና በማጽናት ምዕራፎች ተከፋፍሎ የሚተገበር ነው ብለዋል።
በመጀመሪያው ዙር ስምንት የክልሉ ተቋማት ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስችላቸውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ከጥር/2019ዓ.ም ጀምሮ እነዚህ ተቋማት እና በስራቸው ያሉት ተጠሪ ተቋማት ወደ ትግበራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል።
የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸውን ያላጠናቀቁ ተቋማት በቀሪዎቹ ሁለት ወራት ፈጥነው ማጠናቀቅ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ መኳንንት አደመ በቢሮው ወደ ሪፎርሙ ለመግባት የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
በሰው ኃይል ዝግጅት፣ በተቋሙ መዋቅር፣ በትምህርት ሥርዓቱ ያሉ ችግሮች ተለይተው መመሪያዎችን የማሻሻል እና የዲጂታላይዜሽን አሠራሮችን የማከናወን ተግባራት መሠራታቸውን ገልጸዋል። ሪፎርሙ ለትምህርት ጥራትም ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አጀበ ስንሻው ቢሮው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል። ለአብነትም ለተቋሙ ሠራተኞች እና መሪዎች ግንዛቤ የመፍጠር፣ የአሠራር ማዕቀፎችን የመፈተሽ፣ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የመለየት፣ ምቹ የሥራ አካባቢን የመፍጠር፣ የመሪዎች አቅምን የመገንባት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አንስተዋል።
ሪፎርሙ ሲተገበር ቀልጣፋ የግብርና አገልግሎቶችን ለመስጠት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም ተናግረዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_28_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
