
ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም (አሚኮ) ከጥቅምት እስከ ጥር ያለው ጊዜ መደበኛ የሰብል መሠብሠቢያ ወቅት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በእነዚህ ጊዚያት በኤልኒኖ ተፅዕኖ ምክኒያት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር የሚትሮሎጂ መረጃዎች ያሳያሉ።
የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ሥራ አሥፈፃሚ ሲሳይ ቀለሙ ኤልኒኖ በክረምት ወቅት የዝናብ እጥረትን የሚያስከትል በበጋ ወቅት ደግሞ ዝናብን ይዞ የሚመጣ ክስተት ነው ይላሉ።
በዚህ ምክኒያት ባለፈው የክረምት ወቅት የነበረው የዝናብ መጠን ከመደበኛው በታች እንደነበር ገልጸዋል። ነገር ግን ባለፉት ቀናት አልፎ አልፎ የጣለው ዝናብ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ዳግም ሊመለስ እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉም ብለዋል።
በመኾኑም በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ መክረዋል።
#የሚፈጠሩ ፀሐያማ ቀናትን በመጠቀም ሰብልን በፍጥነት መሠብሠብ፤
#የታጨደውን ምርት ከዝናብ ለመከላከል በአግባቡ መከመር፣ መሸፈን እና መጠበቅ፤
#እርጥበት ለተባይ መራቢያ ምቹ ኹኔታ ስለሚፈጥር ማሳን በንቃት በዕየለቱ መከታተል እንደሚገባ መክረዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
