ከሰብል ሥብሠባ እስከ ጎተራ፤ ለምርት ጥራት ዘመናዊ አሠራርን መተግበር !

4

 

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት እና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ.ር) አሁን ላይ በክልሉ የደረሱ ሰብሎች በመሠብሠብ ላይ መኾናቸውን ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

በድህረ ምርት ወቅት የሚከሰተው የምርት ብክነት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚደርስ በመኾኑ ይህ እንዳይኾን አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ መሠብሠብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

አርሶ አደሮች ወቅቱን ጠብቀው ሰብሉን ካልሠበሠቡ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን ወጭ አድርገው ያለሙት ሰብል በተለያዩ መንገዶች ጉዳት እንደሚደርስበት አስገንዝበዋል።

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መጥቶ ሊያበላሸው ይችላል ነው ያሉት። ሻጋታ በመፍጠርም ምርቱ በተለያየ በሽታ የሚጠቃበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል። ጊዜው ካለፈ በኋላ የሚሠበሠበው ምርትም ለከፍተኛ ብክነት ይጋለጣል ነው ያሉት።

አርሶ አደሮች ከሰብል ሥብሠባ እስከ ጎተራ በሚዘልቀው ሂደት ዘመናዊ አሠራርን መጠቀም ቢችሉ ምርት እንዳይባክን ወሳኝ መፍትሔ እንደኾነም

ገልጸዋል። በተለይም እንደ ኮምባይነር ያሉ የምርት መሠብሠቢያ ቴክኖሎጅዎችን መጠቀም ተገቢ ነው ብለዋል። የማኅበራዊ እሴታችን መገለጫ የኾነውን

የቡድን አሠራር በመጠቀም ሰብልን መሠብሠብ ይገባል ነው ያሉት።

አርሶ አደሮች የምርት መሠብሠቢያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ግብርና ቢሮ ከአበዳሪ ተቋማት ብድር የማመቻቸት እና ማሽኖችን የማቅረብ ሥራ እያከናወነ መኾኑን አብራርተዋል።

የምርት ብክነት በአብዛኛው የሚታየው በማከማቻ ቦታ በመኾኑ ቢሮው ከሦስት ኩንታል እስከ 40 ኩንታል

ምርት መያዝ የሚያስችሉ ዘመናዊ የኾኑ የብረት ጎተራ ማከማቻዎችን ለአርሶ አደሮች እያቀረበ መኾኑንም አንስተዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🇪🇹 የክንደ ብርቱዎች ጽኑ እናት
Next articleበሳምንት 230 ሺህ ጫጩት በማስፈልፈል ለገበያ ለማቅረብ የተዘጋጀው የኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ