
ከተራ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ጀምሮ እስከ ሁቲ አማጺዎች ጥቃቶች ድረስ ለተለያዩ አለመረጋጋቶች የተጋለጠ ነው። 130 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም በማስከበር ረገድ አኩሪ ልምድ አላት። ይህ ልምዷ የባሕር ኀይል አቅም ገንብታ ከጎረቤት ሀገራት ጋር
ብትቀላቀል አካባቢውን ከወንበዴዎች እና ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ለመጠበቅ አቅም ይፈጥራል። በአካባቢው እየተባባሰ የመጣው የኀያላን ሀገራት ወታደራዊ መሠረቶች ግንባታም ለቀጣናው ሉዓላዊነት ስጋት ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር እና የባሕር ኀይል ባለቤትነት የራሷን የንግድ
መስመሮች ከማስጠበቅ ባለፈ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በእኩልነት በመቆም የኀይል መዛባትን በማስተካከል እና የጋራ ደኅንነትን በማረጋገጥ ለቀጣናው ዘላቂ መረጋጋት አስተማማኝ ሚዛናዊነትን ያመጣል። የመካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች መሪ ተመራማሪ አማረ ቀናው
(ዶ.ር) “የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ስትራቴጂ በጂኦፖለቲካዊ ውድድር ውስጥ የባሕር ላይ ጥቅሞችን እና ስልታዊ ራስን በራስ የማሥተዳደር እውን ማድረግ” በተሰኘው ጥናታቸው ይህ ቀጣና በከፍተኛ የጸጥታ እና የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ የሚገኝ ቢኾንም ለኢትዮጵያ በወደብ ልማት፣
በሎጂስቲክስ፣ በኢነርጂ እና በጋራ ጸጥታ ማዕቀፎች ከአጋሮች ጋር የትብብር ድልድይ ለመገንባት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል። የባሕር ላይ ደኅንነትን ማረጋገጥ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የጦር መሳሪያ እና አደንዛዥ ዕፅ ንግድን ለመከላከል ያስችላል።
የኢትዮጵያ የጸጥታ ተቋማት ከቀጣናው የባሕር ጠባቂዎች ጋር በቅንጅት ሲሠሩ የወንጀል አውታሮች ሥር ሰድደው እንዳይስፋፉ ያግዛል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት እና የባሕር ኀይል አቅም መገንባት ለራሷ ብሔራዊ ጥቅም ብቻ አይደለም። የቀይ ባሕር ቀጣናን ከውጭ
ኀይሎች ውድድር እና ከጸጥታ ሥጋቶች ተላቅቆ አስተማማኝ የሰላም እና የትብብር መስመር እንዲኾን ለማድረግ የሚያስችል ቁልፍ ግብዓት ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
