ለዓመታት የተጓተተው መንገድ በዚህ ዓመት ይጠናቀቅ ይኾን?

7
ከተጀመረ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል። የአካባቢው መልክዓ ምድር አቀማመጥ ፈታኝ መኾን፣ የሰሜኑ ጦርነት፣ በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር፣ የተቋራጮች መቀያየር እና ሌሎች ተግዳሮቶች የመንገድ ሥራውን የኤሊ ጉዞ አድርገውት ቆይተዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ–
ጃናሞራ አስፋልት መንገድ የማኅበረሰቡን የመንገድ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ከረዥም ዓመታት በፊት ቢጀመርም ዛሬም ጉዞውን ማገባደድ ተስኖት ይስተዋላል። የሰሜን ጎንደር ዞን መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ መምሪያ ኀላፊ እሸቴ መልኬ ዓመታትን ያስቆጠረው የመንገድ ፕሮጀክት
ዘንድሮ ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ እያሳየ መኾኑን ገልጸዋል። የመንገድ ሥራው ከባለፉት ዓመታት በተሻለ ኹኔታ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። ዞኑ ለፕሮጀክቱ ክትትል እና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር የጎንደር ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ሥራ
አሥኪያጅ ዳንኤል ንጉሴ መንገዱ ከደባርቅ-ቧሂት እና ከበለስ መካነ ብርሃን በሁለት ፕሮጀክት እየተሠራ ነው ብለዋል። ከደባርቅ ቧሂት ያለው ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ እንደቀረው ያነሱት ሥራ አሥኪያጁ አሁን ላይ በሥራ ላይ የሚገኘው ግን የበለስ መካነ ብርሃን ፕሮጀክት መኾኑን ተናግረዋል።
በ2019 በጀት ዓመት ከበለስ መካነ ብርሃን ያለውን መንገድ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ነው ያነሱት። የመንገድ ፕሮጀክቱ 75 በመቶ መድረሱንም ገልጸዋል። የደባርቅ – ጃናሞራ የአስፋልት መንገድ 63 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል።
✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበኤሮ ስፔስ ዘርፍ ሀገሩን ለማስጠራት ርዕይ የሰነቀው ባለ ምጡቅ አዕምሮ
Next articleሕዝቡ ጽንፈኝነትን አውግዟል፤ የሰላም ዘብነቱንም አረጋግጧል።