“የታዩ መልካም አጋጣሚዎችን እናጸናለን” አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)

7

 

​ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ክልላዊ የፓርቲ እና የመንግሥት ተግባራት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪው አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) ባለፉት ወራት የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን በመገምገም ለቀጣዩ አሻጋሪ ዕቅድ መሳካት በርካታ የቤት ሥራዎች የተያዙበት ነበር ብለዋል።

በሩብ ዓመቱ አበረታች የመንግሥት የልማት ሥራዎች መከናወናቸውንም ተናግረዋል። በመኸር ሥራ፤ በምርት እና ምርታማነት ጭማሪ ተግባር እና ከውጭ የሚገቡ ተኪ ምርቶች ላይ አመርቂ ውጤት መገኘቱንም አስገንዝበዋል።

​ተጋላጭ የሚባሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተ ሥራ መሥራት እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል።

የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውን ነው የገለጹት። በቀጣይም ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

​#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_26_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ስንታየሁ ኃይሉ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ጽንፈኝነትን ከልብ መታገል ይገባል” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next article”የሚዲያ ተቋማትን አቅም በስልጠናና በሙያ ስነ ምግባር በማጠናከር ሀሰተኛ መረጃን መከላከከል ያስፈልጋል” የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን