በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች ለምሥራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር የደጀንነት ድጋፍ አደረጉ።

10
በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች እና የከተማ አሥተዳደሮች በቀጣናው ተሰማርቶ ለሚገኘው በሀገር መከላከያ ሠራዊት ለምሥራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር የእርድ ሰንጋ ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉን ያደረጉት የስማዳ፣ የአንዳቤት እና የእስቴ ወረዳዎች እንዲሁም የመካነ ኢየሱስ እና የወገዳ ከተማ አሥተዳደሮች ሲኾኑ ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የእርድ ሰንጋዎችን አስረክበዋል።
የእስቴ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ማንተፋርዶ ሞላ እና የስማዳ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ እንዳልክ ጥላሁን በሰጡት አስተያየት ሠራዊቱ እየፈጸመ ያለው አኩሪ ጀግንነት እና ተጋድሎ ሀገርን እና ሕዝብን የሚያኮራ ነው ብለዋል።
አክለውም ሕዝቡ እና አሥተዳደሮቹ ሠራዊቱን ለማበረታታት እና በማንኛውም አጋጣሚ ከጎኑ መኾናቸውን ለማረጋገጥ ይህንን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የምሥራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል መሐመድ ኢድሪስ በበኩላቸው በጽንፈኛው ቡድን ላይ እየተመዘገበ ላለው ድል የሕዝቡ ከሠራዊቱ ጎን መቆም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። ሕዝቡ አለኝታነቱን ለማሳየት ላበረከተው ድጋፍም አመሥግነዋል። መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በምርት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በደቦ ሰብል እየሠበሠብን ነው።
Next articleአቶ አሕመድ አሊ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ኾነው ተሾሙ።