ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በምርት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በደቦ ሰብል እየሠበሠብን ነው።

7
የፋርጣ ወረዳ ነዋሪዎች አርሶ አደር ብዙአየሁ ሞላ እና አርሶ አደር ደሴ ገላ ከግብርና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ሙያዊ ምክር በመቀበል የደረሱ ሰብሎችን በደቦ በመሠብሠብ ላይ መኾናቸውን ገልጸዋል። ያልደረሱትን ሰብሎችን ደግሞ ሲደርሱ በማኅበር በመደራጀት በፍጥነት ለመሠብሠብ የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦችን በመተግበር ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የተሠበሠበው ምርት ከጎርፍ እና ከዝናብ አደጋ የተጠበቀ እንዲኾን የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ናቸው። ከሰብል ጥበቃው ጎን ለጎን የጎርፍ መከላከያ ሥራዎችን በመሥራት እና የመስኖ ግብዓቶችን በማሟላት ለቀጣይ የምርት ዘመን ዝግጅት እያደረጉም ይገኛሉ።
የፋርጣ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ማዕድነው ብርሃን የደረሱ ሰብሎችን ከመሠብሠብ ባሻገር ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሲከሰት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለቀጣይ የመስኖ ሥራ ዝግጅት ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በወረዳው በዘር ከተሸፈነው ከ36 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ እስካሁን 25 ሺህ ሄክታር የሚኾነው ሰብል መሠብሠቡን አንስተዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ የሽጥላ ፈቃዴ በዞኑ አርሶ አደሮች የምርት ብክነት እንዳይገጥማቸው በግብርና ባለሙያዎች በኩል ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል። በዞን ደረጃ በዘር ከተሸፈነው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 243 ሺህ ሄክታር የሚኾነው ሰብል መሠብሠቡንም ገልጸዋል።
አርሶ አደሮች ዘመናዊ የግብርና አሠራርን እንዲጠቀሙ እየተደረገ መኾኑንም አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡ ተክለብርሃን ፈንታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleታራሚዎችን ወደ ውጤታማ ምርታማነት
Next articleበደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች ለምሥራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር የደጀንነት ድጋፍ አደረጉ።