“ለውጭ ኀይሎች እና ለውስጥ ባንዳዎች ፍላጎት ማስፈጸሚያ አንኾንም” የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች

6

 

በአማራ ክልል የተዘረጋው የሰላም ጥሪን ተቀብለው የሚገቡ የታጣቂዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።

ዛሬም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

‎ወደ ሰላም የተመለሱት ታጣቂዎች የቆዩበት የትጥቅ መንገድ እርስ በእርስ መጠፋፋት መኾኑን በመገንዘብ የሰላም ጥሪውን መቀበላቸውን ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ “የውጭ ኀይሎች እና የውስጥ ተላላኪ ባንዳዎች የፍላጎት ማስፈጸሚያ አንኾንም” ነው ያሉት።

በጫካ በቆዩበት ወቅት በማኅበረሰቡ ላይ ለደረሰው ጉዳት ይቅርታ በመጠየቅ በቀጣይም የፈጸሙትን ጥፋት ለመካስ በሚያስችሉ የልማት ሥራዎች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል። ሌሎች በጫካ የቀሩ የታጣቂ ቡድኖችም የሰላም አማራጩን በመቀበል ወደ ሰላም መመለስ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
‎
ከታች አርማጭሆ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የገቡትን ታጣቂዎች የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተቀብለዋቸዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_24_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“በአንድ እጅ ሰላምን በሌላ እጅ ደግሞ ልማትን ማስቀጠል ይገባል” አቶ ጎሹ እንዳላማው
Next article“ምድራዊ ፈተና በዝቶ፣ ዙሪያው ቢነድ በገሞራ፤ ጥሰን እናልፈዋለን፣ የማይሞት ታሪክ ልንሠራ።” የወታደሩ ዝማሬ