ጥቅምት 24 – የሕገወጡ ሕወሃትን እውነተኛ የጥፋት መልክ ያጋለጠ ቀን!

41
ጥቅምት 24 ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጥቃትን በጀግንነት የመከተበት እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና ህልውና የታደገበት ቀን ኾኖ በታሪክ ይታወሳል። በዕለቱ ሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመው የተንኮል ክህደት የተሞላበት ጥቃት የኢትዮጵያን ሕዝብ
ታጋሽነት እና ፍቅር የፈተነ ብቻ ሳይኾን የቡድኑን እውነተኛ የጥፋት መልክ ያጋለጠ ነበር። ቀኑ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ የሀገሪቱን ሕልውና ለማስጠበቅ የተገደዱበት፣ የሕልውና ዘመቻው የታወጀበት እና የሀገርን ክብር የማስቀደም ጥብቅ ቃልኪዳን የተገባበት ምዕራፍ ነው።
የቡድኑ ፖለቲካ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከመጀመሪያውኑ በውጭ ኃይሎች ፍላጎት የተቃኘ እና የኢትዮጵያን ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ማዳከም ላይ ያተኮረ ነበር። ቡድኑ የኢትዮጵያን ብዝኃነት እና ሰላም እንደ ስጋት በመቁጠር ከታሪካዊ ጠላቶች እና ከውጭ አሻጥረኞች ጋር
በመተባበር ሀገርን ለማተራመስ ሰፊ ሥራ ሠርቷል። የውጭ ኃይሎች ኢትዮጵያን በጉልበት ማንበርከክ ባልቻሉ ቁጥር የውስጥ አሸባሪዎችን እንደ ፈረስ በመጠቀም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ አውታሮች ለማናጋት ሞክረዋል። ቡድኑ የዚህ የውጭ ኀይሎች የጥፋት አጀንዳ
አስፈጻሚ ፈረስ በመኾን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ሲበዘብዝ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የውጭ ኃይሎች የሚሰነዝሯቸውን የዲፕሎማሲ ጫናዎች፣ የሚዲያ ዘመቻዎች እና የኢኮኖሚ ማዕቀቦች በጽናት በመቋቋም ሕዝብን እና ሠራዊቱን በአንድነት
አስተባብረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንባር በመገኘትም የሠራዊቱን ሞራል የገነቡበት እና ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሚለውን አቋም በተግባር ያረጋገጡበት አካሄድ የድሉ ቁልፍ ምሰሶ ኾኗል። የጥቅምት 24 ዕኩይ ተግባር የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት በጠላት ፊት እንዲጠናከር አደረገው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የሀገርን ዳር ድንበር ለመከላከል ያደረገው መስዋዕትነት የውጭ ኃይሎችንም ኾነ የውስጥ አሻንጉሊቶቻቸውን እቅድ አክሽፎታል። የቡድኑ የጥፋት ትርክት እና የወታደራዊ አቅም አከርካሪ የተሰበረው በዚሁ የጽናት እና የጀግንነት ምዕራፍ
ውስጥ ነው። የቡድኑ ውድቀት መፋጠን የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ከውጭ ኃይሎች ሴራ እና ከውስጥ ከሀዲዎች ጋር ያደረጉት የህልውና ትግል ድል ውጤት ነው።
✍️ በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleደብረ ማርቆስ ከተማ ከድኅረ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በኋላ በለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች።
Next articleበባሕር ዳር የሕዝብን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።