“የኃይል አቅርቦት ለአብዛኛዎቹ የልማት ሥራዎች አንቀሳቃሽ ሞተር ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

8

 

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ “የኃይል አቅርቦት ለአብዛኛዎቹ የልማት ሥራዎች አንቀሳቃሽ ሞተር ነው” ብለዋል። በተለይም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፋን ዕድገትና ምርታማነት ለማሻሻል የኃይል አቅርቦት ወሳኝ ግብዓት ስለመኾኑ ተናግረዋል።

ይህንን የኃይል አቅርቦት በተሻለ ሁኔታ ለማግኘት በክልሉ በዕቅድ የተያዙ እና የተጀመሩ የመብራት መሰረተ ልማት አውታሮችን በቅንጅትና በትብብር በመሥራት ማስጀመርና ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

ይህንኑ የክልሉ ሕዝብ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮች ጋር በኃይል አቅርቦት እና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ በአጋጠሙ ችግሮች እና ችግሮቹ በሚፈቱበት አግባብ ዝርዝር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ስምምነት ላይ የተደረሰባቸውን ጉዳዮች በመተግበር የጋራ ግቦችን ለማሳካት እንደሚሠራም ርእሰ መሥተዳድሩ አረጋግጠዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_23_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleከሸዋ ባቄላ እስከ እመጓ ስንዴ!
Next article“አልሚዎችን ለመሳብ እና ኢንቨስትመንትን ለማስፋት የኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት ወሳኝ ጉዳይ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ