ከሸዋ ባቄላ እስከ እመጓ ስንዴ!

2
የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በአማራ ክልል ካሉ ዋና ዋና የግብርና ምርምር ማዕከላት መካከል አንዱ ነው። ማዕከሉ በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች የሚገኘውን የግብርና ሥራዎችን በምርምር በመደገፍ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ደጉ ተመቼ ለአሚኮ እንደተናገሩት ማዕከሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማፍለቅ እና ማላመድ፣ ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ የማስተዋወቅ እንዲኹም የመነሻ ዘር አቅርቦት ላይ መሠረት አድርጎ ይሠራል። ማዕከሉ በርካታ
ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ እና የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት ወደ ልማት ማስገባቱንም ገልጸዋል። የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ በኩል በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በሰብል ምርት እና በአፈር እና ውኃ ጥበቃ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አብራርተዋል።ለአብነትም አርሶ
አደሮችን ተጠቃሚ ያደረጉ ለምግብ እና ከ4 በላይ የቢራ ገብስ ዝርያዎችን በምርምር አውጥቶ በማላመድ ምርት እንዲሰጡ ማድረጉን ገልጸዋል።
“ሸዋ” የሚባል ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ የባቄላ ዝርያ በምርምር አውጥቶ በማላመድ ለውጭ ገበያ በሚኾን የጥራት ደረጃ ጭምር ምርት እንዲሰጥ
ተደርጓል ነው ያሉት። ይህን ዝርያ እስከ ጅማ እና ጎንደር ድረስ በማስፋፋት እየለማ እንደሚገኝ አብራርተዋል።”እመጓ” የሚባል የዋግ በሽታን የሚከላከል፣ ለደጋ እና ለወይና ደጋ አካባቢዎች የሚስማማ፣ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ የስንዴ ዝርያ አውጥቶ ወደ ልማት ማስገባቱንምጠቁመዋል።
በተጨማሪም ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የድንች እና የነጭ ሽንኩርት ዝርያዎችም በምርምር ማዕከሉ ተለቅቀው ወደ ልማት ገብተዋል ነው ያሉት።
በእንስሳት ዘርፉም ከደቡብ አፍሪካ የመጡ በደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ብቻ የሚገኙ የበግ ዝርያዎችን እያለማ እና አርሶ አደሮችን
ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።በአካባቢው የሚገኘውን የቢራ ፋብሪካ ተረፈ ምርት በመጠቀም “ገፈራ” የሚባለውን ዘመናዊ መኖ በማዘጋጀት ማኅበረሰቡ እንዲጠቀምበት እያደረገ መኾኑንም ጠቁመዋል። ይህም ከፍተኛ የወተት ምርት ለማግኘት አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመኾኑ አንስተዋል
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየኢትዮጵያ ኃያልነት ለጎረቤቶቿም በረከት ነው!
Next article“የኃይል አቅርቦት ለአብዛኛዎቹ የልማት ሥራዎች አንቀሳቃሽ ሞተር ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ