አቶ ፀጋው እሸቴ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ተቀዳሚ ዋና አሥተዳዳሪ ኾነው ተሾሙ።

6

 

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 33ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ፀጋው እሸቴን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ዋና አሥተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

አዲሱ ተቀዳሚ ዋና አሥተዳዳሪ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር «የብሔረሰብ አሥተዳደሩን ብሎም የአማራ ክልልን ሁለንተናዊ ሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄ እንዲረጋገጥ ለማድረግ ከሕዝብ ጋር በመኾን በቁርጠኝነት እንሠራለን» ብለዋል።

በአሥተዳደሩ የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ከማጠናቀቅ ባለፈ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእንስሳት ሀብትን፣ የማር ምርትን እና ሌሎች የአካባቢውን እምቅ ፀጋዎች ለማልማት እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_23_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleለሀገር መከላከያ ሠራዊት የተደረገ አጋርነት፤ የዳንግላ ወረዳ አበረታች ድጋፍ።
Next articleየኮዳውን ውኃ በርህራሄ የሚያካፍል – ጀግናም፣ ትሁትም ወታደር!