ክንደ-ብረት፣ ልበ-አንበሳ – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት!

7

 

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር በሚመጥን መልኩ ተገንብቷል። ሠራዊቱ ለሀገር ውስጥ ጸጥታ ብቻ ሳይኾን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሰላም መረጋገጥ የጸና ቁመና እና ከፍተኛ ዝግጁነት እያሳየ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሠራዊቱ በመንግሥታት ለውጥ የማይናወጥ፣ ሀገርን አሻግሮ የያዘ፣ በተለያዩ ግዳጆች በውጤት ተፈትኖ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት የኾነ ትውልድ ተሻጋሪ መኾኑን ተናግረዋል።

ሠራዊቱ በሰላም ጊዜ የልማት አርበኛ፣ ለድንገተኛ አደጋዎች የማይበገር እና ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ሳይንስ መመዘኛዎችን ያሟላ ነው።

በቀጣናዊ እና አሕጉራዊ አውድ ሲታይም ሠራዊቱ ከተለያዩ ሀገራት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ጀምሮ እስከ ቀጣናዊ የተረጋጋ ሁኔታ መፍጠር ድረስ የሰላም ዘብ ኾኖ አገልግሏል።

ሠራዊቱ እንደ ደቡብ ኮሪያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሌሎችም የአፍሪካ አካባቢዎች በተከናወኑ የሰላም ማስከበር ዘመቻዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ይህም ለሰላም ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት በተግባር የሚገልጥ ነው።

ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት እንደ ሱ 30 እና የሱ-35 (Su-35 4++ Generation) የጦር ጄቶች እና የኤስ-400 (S-400) የአየር መከላከያ ሥርዓት ያሉ ዘመናዊ የውጊያ ቴክኖሎጂዎች ታጥቋል። በተጨማሪም በድሮን ቴክኖሎጂዎች፣ በራዳር እና በሳተላይት የመረጃ መረቦች የክትትል አቅሙ ተጠናክሯል።

ሠራዊቱ በሠለጠነ የሰው ኀይል፣ በብቁ መሪዎች፣ በሙያዊ ዲሲፕሊን እና በጥልቅ ተቋማዊ ሪፎርም እየተገነባ ይገኛል። እነዚህም የትኛውንም ውጫዊ እና ውስጣዊ ስጋት በአጭር ጊዜ የመቋጨት ሙሉ አቅም እንዲኖረው ያስችላል።

ሠራዊቱ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰን በመላው አፍሪካ ቀጣና የሰላም፣ የጸጥታ እና የመረጋጋት ዋስትና ኾኖ ዘልቋል።

ኢትዮጵያ የሉዓላዊነቷን መሠረት በምድር እና አየር ኀይል ብቻ ሳትወስን ባሕር ኀይሏንም በማደራጀት እና በማጠናከር ላይ ትገኛለች።

#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#AMECO ​#ENDF ​#PeacekeepersOfAfrica
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_22_2019_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።
Next articleባዲገዝ – የወሎየዎች ተሳስቦ የመኖር አንዱ እሴት