
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የቀበሌዎችን ደረጃ ለማዘመን የተሠራውን የልቼ ቀበሌ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤትን፣ የደብረ ብርሃን ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጄክትን፣ የደብረ ብርሃን የኮሪደር ልማትን እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሕንጻ ግንባታን ነው መርቀው ሥራ ያስጀመሩት።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከተሞችን ውብ፣ ለነዋሪዎች እና ለጎብኝዎች የተመቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ጽዱ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ እንዲኖር እንዲህ አይነት ሥራዎች አስፈላጊ መኾናቸውንም ገልጸዋል። የፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጄክቱ ጽዱ ከተማን ለመፍጠር እንደሚያስችልም ተናግረዋል። የተሠሩትን ፕሮጄክቶች በአግባቡ መጠበቅ እንደሚገባም አመላክተዋል።
ፕሮጄክቶቹን ሠርተው ለፈጸሙ ሁሉ ምሥጋናም አቅርበዋል። በፍሳሽ ማጣሪያው ውስጥ የሚቀሩ ሥራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የተሠሩ ሥራዎችን በአግባቡ መጠቀም ደብረ ብርሃንን የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት መስጫ ከተማ ማድረግ ያስችላታል ነው ያሉት።
የልቼ ቀበሌ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ግንባታ የከተማ አሥተዳደሩ ሕዝብን ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት፣ ሕዝብ በዘመናዊ ተቋም ለመገልገል ያለውን ፍላጎት እና ድጋፍ ያሳየበት መኾኑንም ተናግረዋል። ግንባታው ዘመናዊ መኾኑንም አንስተዋል።
#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_22_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
