
ኢትዮጵያ ለግብርና የተመቸ ለም አፈር፣ ሰፊ የውኃ ሃብት፣ ተስማሚ አየር እና አምራች የሰው ኀይል የታደለች፤ ግብርናን ለዓለም ያስተዋወቀች ሀገር ናት።
ይሁንና እነዚህን ተፈጥሯዊ ጸጋዎች በዓመት ሁለት እና ሦሥት ጊዜ ማልማት ሲቻል የእርሻ ሥራው ለረጅም ዘመናት በክረምት ዝናብ ላይ ብቻ ጥገኛ በመኾኑ ኢትዮጵያ ለዓመታት የሚገባትን ምርት ሳታገኝ ኖራለች።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ አቅምን አሟጥጦ መጠቀም አስፈልጓል። ለዚህም ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት በማስወጣት መሬትን በመስኖ ታግዞ ማልማት እና ምርታማነትን የማሳደግ ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ተግባር ተገብቷል።
ይህንኑ ሀገራዊ ራዕይ መሠረት አድርጎ ላለፉት ዓመታት ሰፊ ጥረት ያደረገው የአማራ ክልል በ2019 ዓ.ም የበጋ ወራት ከ734 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት አቅዶ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
ክልሉ በመስኖ ሊለማ የሚችል 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር እምቅ የመሬት ሃብት ቢኖረውም እስካሁን በዘመናዊ መስኖ የለማው ጥቂት ብቻ በመኾኑ ዘንድሮ ለሚከናወነው የመስኖ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶታል።
በዚህም መሠረት በበጋ መስኖ ከሚታረሰው መሬት ውስጥ 250 ሺህ ሄክታሩ አዲስ ወደ መስኖ ልማት የሚገባ መሬት ነው።
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከመስኖ ልማት ከ95 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ግብ ተቀምጧል። ይህ በክረምት ወቅት የሚካሄደውን የእርሻ ልማት በእጅጉ የሚያግዝ ይኾናል።
የ2019 የበጋ መስኖ ልማት ዕቅድን ውጤታማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዙ የተለያዩ ተግባራትም እየተከናወኑ ይገኛሉ።
👉 ጅምር የመስኖ ግድቦችን ማጠናቀቅ እና አዳዲስ የመስኖ አውታሮችን ወደ ሥራ ማስገባት
👉 የተለያዩ የገጸ ምድር የውኃ አማራጮችን አሟጥጦ መጠቀም
👉 የውኃ መሳቢያ ሞተሮችን ለአርሶ አደሮች ማቅረብ
👉 ምርታማነትን የሚጨምሩ የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት እና ስርጭትን በሰፊው ማካሄድ ይገኙበታል።
👉 ከስንዴ በተጨማሪ የተለያዩ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን የማልማት ሥራ ይከናወናልም ተብሏል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ገቢን ያማከለ የመስኖ ልማት ሥራ ክልሉ ካለው ሰፊ እምቅ የመልማት አቅም አኳያ ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#አሚኮ #መስኖ_ልማት #ግብርና #አማራ_ክልል
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
