
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ትግሉ ዓላማ የሌለው እና ለሕዝብ የማይጠቅም መኾኑን ተረድተናል ብለዋል።
የትጥቅ ትግል የተሳሳተ አካሄድ መኾኑን ገልጸዋል። ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ትግሉ ፋይዳ የሌለው መኾኑን ተረድተው ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉትን ታጣቂዎች የታች አርማጭሆ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እና በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከለካያ ሠራዊት መሪዎች አቀባባል አድርገውላቸዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
