🌱 ምርጥ ዘር:- የግብርና ምርታማነት፣ የምግብ ዋስትና እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት!

2

 

በምግብ ሰብል ራስን በመቻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን የቴክኖሎጂ ግብዓትን ተጠቃሚነት ማሳደግ ወሳኝ ነው።

ምርጥ ዘርን መጠቀም ደግሞ ምርታማነትን በማሳደግ እና ድህነትን ለመቀነስ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የአማራ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት መረጃ እንደሚያረጋግጠው ምርጥ ዘርን መጠቀም ብቻውን ከ30 እስከ 50 በመቶ የምርት ዕድገት ያስገኛል።

የድቃይ በቆሎ ምርጥ ዘርን ከታዘዘው ማዳበሪያ እና ፀረ-ተባይ ጋር በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ምርታማነቱ በሄክታር 60 ኩንታል እንደሚደርስ ያስረዳል። በአካባቢ ዘር የሚገኘው ምርታማነት ከ30 ኩንታል እንደማይዘልም ይገለጻል።

ምርታማነት ብቻውን ተጠቃሚነትን አያረጋግጥም። ለዚህም ነው መንግሥት አርሶ አደሮች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጡ የገበያ ትስስር መፍጠርን ትኩረቱ ያደረገው።

ከፍተኛ ምርት የሚፈልጉ አግሮ ኢንዱስትሪዎች በየጊዜው እየተስፋፉ መምጣታቸው፣ የውጭ ገበያ ፍላጎትን ማሟላት የሚችሉ ምርቶች ላይ ትኩረት መደረጉ ምርታማነትን በምርጥ ዘር ለማሳደግ ገፊ ምክንያቶች እንዲኾኑ አድርገዋል። እንደ ስንዴ ያሉ ምርቶችን በራስ አቅም በመሸፈን ከውጭ ማስገባት ማቆም መቻሉ አንዱ ተጨባጭ ውጤት ነው።

ምርጥ ዘር የምርታማነት መሠረት ነው የሚባለው ድርቅን እና በሽታዎችን መቋቋም፣ የዕድገት ዑደትን ማሳጠር እና ጥራትን ማረጋገጥ በመቻሉ ነው።

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ተቋማት በየጊዜው ባደረጓቸው ጥናቶች ለተለያዩ ሥነ-ምኅዳሮች የሚስማሙ እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ እና ባቄላ ዝርያዎችን ለኅብረተሰቡ አበርክተዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም

#AMECO #Seed_Technology #Productivity #Ethiopia

✍️ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሑዋዌ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያዩ።
Next article“ሌሎችም የሰላም አማራጭን መቀበል አለባቸው ” የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች