ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሑዋዌ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያዩ።

14

 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሑዋዌ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በኢትዮጵያ የሑዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመኾን በቅርቡ ሥራ ከጀመሩት ኤሪክ ዩዋን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በውይይታችንም መንግሥት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ለማስቀጠል እና ለማፋጠን እየሠራቸው ያሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎች እጅግ አበረታች መኾናቸውን ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ገልጸውልኛል ነው ያሉት።

ሑዋዌ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እና ብሔራዊ የልማት ግቦቻችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ውስጥ በተለይም በአይሲቲ መሠረተ ልማትና በግንኙነት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞም ከሑዋዌ ጋር በትብብር፣ በብሔራዊ ባለቤትነት፣ በዘላቂነት፣ በደኅንነት እና በአካባቢያዊ እሴት ፈጠራ መርኾዎች ላይ ተመሥርተው በሚሠሩባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ እየተጓዘ ባለበት በዚህ ወቅት ሑዋዌም ለዚህ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እና ያለንን የሥራ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleለመንገድ ፕሮጀክቶች በክልሉ መንግሥት ከተያዘው በጀት በተጨማሪ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ከኅብረተሰቡ ተሠብሥቧል።
Next article🌱 ምርጥ ዘር:- የግብርና ምርታማነት፣ የምግብ ዋስትና እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት!