
የአማራ ክልል መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ቢሮ የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ አቅጣጫ የውይይት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እያካሄደ ነው።
የክልሉን ዕድገት ለማፋጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንገድ እና ትራንስፖርት ዘርፉ ሚና ከፍተኛ ነው።
የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የመንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ እና የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን የተሳለጠ የሎጂስቲክስ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል በትኩረት እየሠራ መኾኑን የቢሮው ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ለሚገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች በክልሉ መንግሥት ከተያዘው በጀት በተጨማሪ ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ከኅብረተሰብ ተሳትፎ መሠብሠቡንም ገልጸዋል።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለይቶ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ባለድርሻ አካለት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል።
የትራንስተፖርት አቅርቦትን ለማስፋፋት እና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማዘመን እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል።
በበጀት ዓመቱ የሎጂስቲክስ አቅርቦትን ለማፋጠን እና የመናኸሪያ፣ የደረቅ ወደብ፣ የተርሚናል እና የፓርክ ግንባታዎችን ለማከናወን መታቀዱም ተመላክቷል።
በዕቅድ የተያዙ ሥራዎችን በትኩረት ለማከናወን ወደ ተግባር ምዕራፍ መገባቱንም ተናግረዋል።
ኀብረተሰቡ እስካሁን ያሳየው ተሳትፎ አበረታች ነው ያሉት ኀላፊው ንቅናቄው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የዘርፉ መሪዎች እና ባለሙያዎች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ደሴ #ጥቅምት_21_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ፦ አሊ ይመር
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
