
ሩሲያ ዓለም አቀፍ ሕጎችን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላማዊ የኒውክሊየር ልማት እየደገፈች መኾኗን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አስታውቀዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ 3ኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ አስመልክተው ከአፍሪካ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የአፍሪካ ሀገራት ከኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ሩሲያ እንደ ኢትዮጵያ ካሉ ሀገራት ጋር በትብብር እየሠራች መኾኑን አብራርተዋል።
ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የመሠረተችው ግንኙነት መከባበርን፣ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ የሀገራቱን ፍላጎት እና ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል ያደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር በሰላማዊ የኒውክሊየር ልማት ላይ በተጀመረው ትብብር የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን አቅም ማብቃት ትኩረት የተሰጠው ዋና ጉዳይ መኾኑንም ተናግረዋል።
ኢቢሲ እንደዘገበው ሀገራቸው በዚህ ዘርፍ ያላትን ሰፊ አቅም እና ልምድ ለማካፈል ሙሉ ዝግጁ መኾኗንም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
