የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በሚደግፈው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የሚሳተፉ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ መውጣት ጀምረዋል።

17
በባሕር ዳር ከተማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ፤ የውጭ እና የውስጥ የሀገር ጠላቶችን የላኪነት እና የተላላኪነት ጥፋት ደግሞ የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ዬደረጋል። ነዋሪዎቹም ከከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች ወደረደባባይ መውጣት ጀምረዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት “ከራስ በፊት ለሀገር” በሚል ጥልቅ የሀገር ፍቅር እሳቤ ውድ ሕይወቱን እየገበረ፤ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ፤ መስዋዕትነት እየከፈለ ሀገሩን እና ሕዝቡን በጀግንነት እየጠበቀ የሚገኝ የሀገር ዘብ ነው።
ኢትዮጵያን ከውስጥ እና ከውጭ ጠላቶች እየተከላከለ ሉዓላዊነቷን አስከብሮ ዳር ድንበሯን እየጠበቀ አለኝታነቱን በጀግንነት እየተወጣ ቀጥሏል። ለዚህ ጊዜ የማይሽረውና ተመን ለሌለው ባለውለታ ሕዝቡም ከጎኑ መኾኑን በሰላማዊ ሰልፍ ድጋፉን እየገለጸ ይገኛል።
ዛሬም የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን የጠበቀ ደጀንነት እና ድጋፍ ለመግለጽ በጠዋቱ ወደ አደባባይ እየወጡ ይገኛሉ።
✍️ ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleግዙፍ የማምረት አቅምን ይዞ የሚገነባው ዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ የዘርፉ ችግር መፍትሔ ለመኾን እየተቃረበ ነው።
Next article“መከላከያ ሠራዊታችን የኅብረ ብሔራዊነታችን ማሳያ አርማችን ነው” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች