
ቢሮው የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅድ ዝግጅት እና ትግበራን እውን ለማድረግ ከተቋማት ጋር የአምስትዮሽ የጋራ ሥምምነት ሠነድ ተፈራርሟል።
ሥምምነቱ ከግብርና ቢሮ፣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለ ሥልጣን፣ ከኅብረት ሥራ ኮምሽን እና ከእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ ጋር የተደረገ ነው።
ሥምምነቱ የመሬት አጠቃቀምን ለማዘመን፣ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የመሬት ሀብትን በፍትሐዊነት እና በዘላቂነት ለመጠቀም፣ ከተበታተነ አሠራር ለመውጣት እና በመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መኾኑ ተገልጿል።
በሥምምነቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ(ዶ.ር) ተገኝተዋል።
#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_15_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
