
12ኛው የጣና ከፍተኛ የአፍሪካ ጸጥታ ፎረም “በአፍሪካ ወደ ሰላም የሚወስዱ መንገዶች፡ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት እና ጂኦፖለቲካዊ ለውጥ” በሚል መሪ መልዕክት በባሕርዳር እየተካሄደ ነው።
በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን የቴክኖሎጂ ሊዓላዊነትን ሳናረጋግጥ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንችልም ብለዋል። ለዜጎቻችን ቴክኖሎጂን ሳናመጣ፣ በክህሎት ሳናሳድግ፣ ከውጭ ቴክኖሎጂ እየጠበቅን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን አናመጣም፣ ካለንበትም ወደፊት መራመድ አንችልም ነው ያሉት።
አፍሪካን የሚገነባ፣ የአፍሪካን ልጆች የሚቀርጽ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል። አፍሪካ ወደኋላ መለስ ብላ እንዴት መገንባት እንዳለባት ማሰብ አለባት ነው ያሉት። አፍሪካ ሀገር በቀል የኾነ የራሷን ቴክኖሎጂ መፍጠር እና መጠቀም እንዳለባትም አመላክተዋል።
የቴክኖሎጂ ጥገኛ እስከኾንን ድረስ የምንፈልገውን ስኬት ማምጣት አንችልም ነው ያሉት። ነጻ የንግድ ቀጣና ሳንፈጥር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንችልም፤ የአህጉሪቱን ዕድግትም ማፋጠን እንችልም ብለዋል።
ስለ ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ከመነጋገራችን አስቀድሞ ስለ ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት መነጋገር አለብን፤ ያለ ቴክኖሎጂ ወደፊት ብዙ አንራመድም ነው ያሉት።
ሰላም እና ልማት የተሳሳሩ ናቸው፤ ግጭት የሚወለደው የሃብት ሽሚያ ሲኖር ነው፤ ሰላም እና ጸጥታ ሳይኖር የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም ብለዋል። ገንዘብ ፈሪ ነው ይባላል፣ ምክንያቱም ግጭት ካለ ገንዘብ ይሸሻል፣ ዕድገት ይጠፋል ነው ያሉት።
ግጭት ሲኖር የውጭ ኀይሎች ለተፋላሚ ኀይሎች መሳሪያ እየሸጡ ሀገርን ይጎዳሉ ብለዋል።
#TanaForum #AfricanSecurity
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_15_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
