
119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኀላፊ ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ የታጠቀ ኀይል ታሪክ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕልውናውን ያቆየውም አንድነቱን እየጠበቀ ከውጭ የሚነሱ ወራሪዎችን ተባብሮ አሳፍሮ በመመለሱ መኾኑን ተናግረዋል።
የዛሬው በዓል ሲከበር 119 ዓመታት ያሳለፈው የሠራዊቱ ግንባታ መሠረት የተጣለበትን ዕለት ለማሰብ ያለመ መኾኑን ጠቁመዋል።
ዘመናዊ ሠራዊቱም ቢኾን ኢትዮጵያን ለማቆየት ከፍተኛ መስዋትነትን የከፈለ ቢኾንም በውጭ ወራሪዎች እና በውስጥ ኀይሎች የመበተን አደጋ ተጋርጦበት እንደነበር አመላክተዋል።
የለውጡ መንግሥት ከመጣ በኋላ ግን የታሪክ ቅብብሎሽ የኾነውን የአኩሪ ገድል ባለቤቱ የሠራዊቱ ቀን እየተከበረ መቀጠሉን ተናግረዋል።
የዘንድሮው በዓልም “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ መልዕክት በግንባርም ኾነ በደጀን እየተከበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_15_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
