
12ኛው የጣና ከፍተኛ የአፍሪካ ጸጥታ ፎረም “በአፍሪካ ወደ ሰላም የሚወስዱ መንገዶች፣ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጥ” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
በፎረሙ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርን መልዕክት ያቀረቡት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር
አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጣና ፎረም ለሚያደርጉት ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።
የአፍሪካ ሰላምን ለማረጋገጥ አሕጉሪቱ መጋፈጥ የሚገባት ጉዳዮች አሉ ያሉት ምክትል ሊቀመንበሯ የአፍሪካን ሰላም ለማረጋገጥ ተግባራዊ እርምጃዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል። የአፍሪካን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ለአፍሪካ ቅድሚያ በመስጠት መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል። የአጀንዳ 2063 የበለጸገች አፍሪካን እውን ማድረግ እና የአፍሪካን አንድነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ማድረጉን ተናግረዋል። ሕዝብ ሰላም ባለው ልማት እንዲኖር መሥራት ይገባልም ነው ያሉት።
የአፍሪካን ሀብት ለአፍሪካ ዕድገት መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል። የአፍሪካን ሀብት ማሠባሠብ፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ማስቆም እና የአፍሪካን ዕድገት ማረጋገጥ ያስፈልጋልም ነው ያሉት። የአፍሪካን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ስጋቶች ድንበር የሚሻገሩ በመኾናቸው ምላሾቻችንም አሕጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መኾን አለባቸው ነው ያሉት። አፍሪካ ክህሎቶች፣ መሠረተ ልማት እና ጠንካራ ተቋማት እንደሚያስፈልጓትም ገልጸዋል።
አህጉራዊ ሥራዎቻችን ለዜጎቻችን ሕይወት መኾናቸውን ማረጋገጥ አለብን ነው ያሉት። የአፍሪካን ነጻ የንግድ ቀጣና ኮሪደሮች እንዲገነቡ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።
አፍሪካ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮች ማስቀደም፣ ተለዋዋጭ በኾነችው ዓለም ውስጥ ጠንካራ ኅብረት እና ግልጽ ዓላማ ሊኖረን ይገባል ነው ያሉት። ውይይቱ በጋራ መተማመን ላይ ሊመራ እንደሚገባም ተናግረዋል።
#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
