
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በባሕር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 12ኛው ጣና ፎረም መድረክ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል። የመልእክታቸው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
“የሰላም መንገዶች በአፍሪካ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 12ኛው የጣና ከፍተኛ የደህንነት ፎረም ላይ ተገኝቼ ንግግር በማድረጌ ደስታ ተሰምቶኛል።
የጉባኤው መሪ ቃል ልንዘነጋው የማይገባንን እውነታ ያሳያል፤ ከድንበራችን ባሻገር የሚወሰኑ ውሳኔዎች በዜጎቻችን፣ በኢኮኖሚ ዕድሎቻችን እና በደህንነታችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። እያንዳንዱን ድንገተኛ ቀውስ መቆጣጠር ባንችልም፣ የመቋቋም አቅማችንን ግን ማጠናከር እንችላለን። ይህ ለአፍሪካ የሀገር በቀል መፍትሄዎችን ማዘጋጀት፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማጠናከር እና ትብብርን ማሳደግ ማለት ነው። አፍሪካ እየተለወጠ ካለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ጋር መላመድ ብቻ ሳይሆን፣ ሥርዓቱን የመቅረጽም ሚና ሊኖራት ይገባል።
ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ቀዳሚና እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ይህም ዜጎችን መጠበቅ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማክበር እና ለውይይት በርን ክፍት ማድረግን ይጠይቃል። ለብሔራዊ ምክክር ባለን ቁርጠኝነት፣ የሰላምን መንገድ የሚመርጡትን ሁሉ ለመቀበል ሁልጊዜም ዝግጁ ነን።
የመደመር ፍልስፍና፣ ጥንካሬዎቻችንን እና አቅማችንን በማስተባበር እንዲሁም ከራሳችን ተጨባጭ እውነታዎች የተቀዱ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ላይ ያተኮረ መሆኑን ያስገነዝበናል። ለወደፊት ትውልዶቻችን የምናወርሳትን ዓለም ለመቅረጽ የላቀ ሚና እየተጫወትን፣ ጠንካራ የመቋቋም አቅም ያላት፣ ሰላማዊ እና የበለጸገች አህጉር መገንባት እንችላለን።
#TanaForum #AfricanSecurity
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ !
