አፍሪካውያን መሪዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ ከተማዋ ባሕር ዳር ተገናኝተው እየመከሩ ነው።

23

 

12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ምሁራን በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም “የሰላም መንገዶች በአፍሪካ – የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካዊ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

በጉባኤው ወቅት ተሳታፊዎቹ በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማስፈን፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንዲሁም ፈጣን ለውጥና ሽግግር በማሳየት ላይ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ አፍሪካ ሊኖራት ስለሚገባው ስትራቴጂካዊ ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሰፊው ይመክራሉ።

#TanaForum #AfricanSecurity
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ !

Previous articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ክቡር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በባሕር ዳር ተቀበሉ።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የጋና ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ ሊቀመንበር ክቡር ጆን ድራማኒ ማሃማን በባሕር ዳር ተቀበሉ።