ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብርናን በቴክኖሎጂ መደገፍ ይገባል።

10

 

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ የበጋ መስኖ ስንዴ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ ከተረጂነት ለመላቀቅ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚውን በቴክኖሎጂ ማዘመን ይገባል ብለዋል።

የስንዴን ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ከፍጆታ አልፎ ለገበያ ለማቅረብ በበጀት ዓመቱ በትኩረት እንደሚሠራም አስረድተዋል።

የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችንም የአርሶአደሮችን ምርታማነት እንዲጨምር በሚያስችል ሁኔታ መሥራት ይገባል ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ ጀማል አሊ በምርት ዘመኑ ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ለመሸፈን ታቅዶ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ጠቁመዋል።

በቂ የዘር እና የማዳበሪያ አቅርቦት ዝግጅት በመደረጉም የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

በመስኖ የሚለማው መሬት በሙሉ አቅም ወደምርት እንዲገባ የውኃ አማራጮችን ለማስፋትም ይሠራል ነው ያሉት ኀላፊው።

የወረዳ የግብርና የሥራ ኀላፊዎችም ከባለፈው ዓመት የተሻለ ለማምረት ከወዲሁ የመሬት ልየታ እና የእርሻ ጅማሮ ሥራ እያከናወኑ መኾኑን ጠቁመዋል።

#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ከሚሴ #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article💎 ማዕድን ልማት – የአማራ ክልል የመጪው ዘመን የንጋት አብሳሪ
Next article🌍 የአፍሪካ የነጻነት ፋና !