💎 ማዕድን ልማት – የአማራ ክልል የመጪው ዘመን የንጋት አብሳሪ

26

 

የአማራ ክልል በምድር ከበለጸጉ እና ከማዕድን ሀብታቸው ተጠቃሚ መኾን ከሚገባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ ነው።

የክልሉ እምቅ ሀብት በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንቶ ባለመያዙ በወርቅ፣ በኢንዱስትሪ ግብዓቶች እና በተለያዩ ተጓዳኝ ውድ ማዕድናት ታጅቦ ሳለ በድህነት አዙሪት ውስጥ እንዲቆይ ኾኗል።

🔬 የጂኦሎጂካል ስርጭት እና የሀብቱ ስፋት:-

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ ትምህርት ቤት ዲን እና የማዕድን እና ሥነ ምድር ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ ምንያህል ተፈሪ (ዶ.ር) ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ በክልሉ በሜታሞርፊክ፣ በደለል ክምችት እና በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተፈጠሩ ሦሥቱም የአለት ስርጭቶች በስፋት ይገኛሉ ብለዋል።

ከቀድሞው አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ክልሎች የትኩረት ማዕከል በተለየ መልኩ በወንበርማ፣ በጓንጓ፣ ከእናርጅና እናውጋ እስከ መካነ ሰላም ባሉ አካባቢዎች በርካታ ውድ እና ተፈላጊ ማዕድናት መኖራቸው በጥናት ተረጋግጧል ነው ያሉት።

💎 የተረጋገጡ ማዕድናት:-

👉 የወርቅ፣ የፓይራይት፣ የኮፐር፣ የሊድ እና የዚንክ ክምችቶች በስፋት የሚገኙበት ክልል ነው።

👉 ከ15 በላይ ሲሚንቶ ፋብሪካዎችን መገንባት የሚያስችሉ እንደ ሳንድ ስቶን፣ ላይም ስቶን እና ጂፕሰም ያሉ የኢንዱስትሪ ማዕድናት በካርታ እንደኾኑ በምርምር ተረጋግጠዋል።

⚠️ የቴክኖሎጂ ድህነት እና የአሥተዳደር ክፍተቶች:-

ይህን ሁሉ ውድ ሀብት አግኝቶ በባለቤትነት መጠቀም ባለመቻል ለዘመናት የቆየው የቴክኖሎጂ ድህነት የላብራቶሪ ምርመራዎችን ለውጭ ሀገር አሳልፎ መስጠት፣ የተሟላ የዳታቤዝ፣ የወጪ እና ጥቅም ትንተና አለመኖር ሀብቱ ለሕዝብ እና ለመንግሥት ዕድገት እንዳይውል አድርጎታል።

🛠️ የቀጣይ አቅጣጫ:-

ማዕድን መገኘቱ ብቻውን ፋይዳ ስለሌለው የጂኦፊዚካል፣ የጂኦኬሚስትሪ እና መሰረታዊ የካርታ ሥራዎችን በማቀናጀት ጥራቱን እና መጠኑን አጥንቶ ለአልሚዎች ማቅረብ የዚህ ዘመን ትውልድ ቀዳሚ ኀላፊነት ነው። ጥሬ ማዕድንን ያለ እሴት ማዕቀፍ መሸጥን ማስቀረትም ይገባል ነው ያሉት።

መንግሥት፣ ሕዝቡ እና ዩኒቨርሲቲዎች በቅንጅት በመሥራት ከቁጥጥር ውጪ የኾነውን ፍቃድ እና የቴክኖሎጂ እጥረት መፍታት አለባቸውም ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#MineralWealth ​#EconomicGrowth #አሚኮ ​#Amhara

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም

✍️ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ዘመናዊ የመሬት አሥተዳደር ሥርዓት ብልሹ አሠራርን እና የሙስና ችግርን የሚፈታ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
Next articleምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብርናን በቴክኖሎጂ መደገፍ ይገባል።