🌍 የአፍሪካ የነጻነት ፋና !

17

 

የጣና ፎረም አፍሪካውያን የውጭ ተጽዕኖን በማስወገድ “አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች” በሚለው መርሕ ላይ ተመስርተው በሰላም፣ በደኅንነት እና በልማት ጉዳዮች ላይ የሚመክሩበት ዓመታዊ አሕጉራዊ መድረክ ነው።

የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ መድረኩ መሪዎች የራሳቸውን መፍትሔ የሚያመነጩበት፣ አፍሪካን ከዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚያስተሳስር እና አጀንዳዎቿን ለዓለም የምታስተዋውቅበት ታላቅ ምሕዳር ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ፎረሙን ለየት የሚያደርገው የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን አንደበት በይፋ የሚንጸባረቁበት መኾኑ ነው ብለዋል።

ከአፍሪካውያን ሀገር በቀል የዛፍ ሥር ውይይት ልምድ የተቀዳው የጣና ፎረም አወቃቀር ነጻ የሐሳብ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ አፍሪካ ወቅታዊ የፖለቲካ ተለዋዋጭነቶችን በትክክል እንድትረዳ ያግዛታል። ከችግሮቿ መነሻዎች ጋር እንድትጋፈጥ በሀገራት መካከል ያለውን መተማመን እንድታጠናክር ያስችላል።

ጣና ፎረም የአፍሪካን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በማጠናከር፣ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

ከአቅም ግንባታ እና ከእርስ በእርስ መረዳዳት አንጻር ሲታይ አፍሪካውያን ሀገራት ያላቸውን ሃብት፣ ዕውቀት እና ልምድ እንዲጋሩ ያደርጋል።

የጣና ፎረም የአፍሪካን የሰላም አስከባሪ ኃይሎች፣ የጸጥታ መዋቅር እና የልማት ስልቶች በማቀናጀት የውስጥ አቅምን ለመጠቀም የሚያስችል መሠረትን ይጥላል።

አሕጉሪቱ ሉዓላዊነቷን እና ራስን የመቻል መንፈሷን እንድታጠናክርም ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል።

​#TanaForum #አሚኮ
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ !

Previous articleምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ግብርናን በቴክኖሎጂ መደገፍ ይገባል።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ክቡር ኢቫሪስት ንዴሺሚዬን በባሕር ዳር ተቀበሉ።