ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ ፕሬዝዳንቶች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

12

 

ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ከጣና ፎረም ጎን ለጎን የአሕጉሪቱን የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመሩ ፕሬዝዳንቶች እና ተወካዮች የሚሳተፉበትን የፕሬዝዳንቶች ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ “አፍሪካ የሌሎችን ሀገራት ዕውቀት እና ቴክኖሎጂ ከመቀበል ወይም ሸማች ከመኾን ወጥታ ችግሮቿን የሚፈቱ አዳዲስ ዕውቀቶችን እና ግኝቶችን እራሷ ማፍለቅ መቻል አለባት” በሚል ርዕስ ነው እየተደረገ ያለው።

የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ከዕውቀት ተጠቃሚነት ወደ ዕውቀት አምራችነት የሚሸጋገሩበት መንገድ፣ የምርምር አጀንዳዎችን የሚወሰነው ማን እንደኾነ፣ የዩኒቨርሲቲ እና የኢንዱስትሪ ትስሰር፣ በዓለም አቀፍ አጋርነቶች፣ በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና በመረጃ አሥተዳደር ላይ የዩኒቨርሲቲ መሪዎች ሊያስቀምጧቸው የሚገቡ መሠረታዊ ሁኔታዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

በውይይቱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር)፣ የአፍሪካ ምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ጆን ጂያፖንግ፤ የሀርጌሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አሕመድ (ዶ.ር)፤ የዛንዚባር ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሰዒድ አል ሃማንን ጨምሮ የጣና ፎረም ተሳታፊ ምሁራን፣ የዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፍ ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የመገጭ ግድብ ለጎንደር ከተማ እና አካባቢው ማኅበረሰብ የልማት ገጸ በረከት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleየጣና ፎረም አካል የሆነው የልዩ መልዕክተኞች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።