“የመገጭ ግድብ ለጎንደር ከተማ እና አካባቢው ማኅበረሰብ የልማት ገጸ በረከት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

18

 

የመገጭ ግድብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተመርቋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ “የመንግሥትን ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈስሶበት ለጎንደር ከተማ እና አካባቢው ማኅበረሰብ የተበረከተ የልማት ገጸ በረከት ነው” ብለዋል።

ፕሮጄክቱ የጎንደር ከተማን የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት የሚያቃልል ይኾናል ብለዋል።

ከቀጥተኛ ጥቅሙ በተጨማሪም ለዓሣ ሃብት ልማት፣ የወንዝ ዳር ልማትን መሠረት አድርገው ለሚገነቡ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች መስፋፋት እና ለከተማዋ ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ በመኾን የሚያገለግል ስለመኾኑም ጠቁመዋል።

በቀጣይም የአካባቢው አርሶ አደሮችን በፍጥነት ወደ ዘመናዊ የመስኖ ልማት ማስገባት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል። በግድቡ የሚለማው የመስኖ ልማትም ለፍጆታ ብቻ የሚውል ሳይኾን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በማምረት ለኢንዱስትሪ ግብዓት እና ለውጭ ገበያ የሚውሉ ምርቶችን ለማምረት ከወዲሁ መዘጋጀት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጀምሮ አለመጨረስን ከኢትዮጵያ መልክነት የፋቁ ፕሮጀክቶች
Next articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ ፕሬዝዳንቶች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።