“ሕዝቡ በውኃ እጥረት እየተቸገረ አንድ ፕሮጄክት ለዓመታት አለመጨረስ እርግማን ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

10

 

የመገጭ ግድብ ፕሮጄክት ከበርካታ ዓመታት በኋላ ግንባታው ተጠናቅቆ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት በነበረው የግንባታ አፈጻጸም ወቅት በአግባቡ እየተከናወነ እንዳልነበረ ጠቁመዋል።

“ለ19 ዓመታት ብዙ ገንዘብ እየባከነበት፣ ሕዝቡ በውኃ እጥረት እየተቸገረ አንድ ፕሮጄክት መጨረስ አለመቻል እርግማን ነበር” ብለዋል። ይህም መጥፎ ልምምድ መኾኑን ገልጸዋል። ይህንን እርግማን ነቅሎ ወደ በረከት ለመቀየር ሥራ ተቋራጭ እስከመቀየር የደረሰ እርምጃ መወሰዱን አንስተዋል።

በዚህም ለጎንደርም፣ ለግድቡም የማይመጥን የነበረውን ሥራ በመቀየር በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቅቆ ለምረቃት በቅቷል ነው ያሉት። አንድን ሥራ ጀምሮ ለፍሬ ማብቃት ልምምዳችን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጄክትን ከጀመሩ በወቅቱ መጨረስ እና ለሕዝብ የገቡትን ቃል በተግባር መፈጸም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የግድቡን መጠናቀቅ ተከትሎ ለጎብኝዎች መዳረሻ እንዲኾን የሚያስችል በግድቡ አካባቢ የጎርጎራ አይነት ፕሮጄክት መገንባት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የውኃ ጥም ሊቆረጥ ይኾን?
Next articleአፍሪካውያን መሪዎች ስለ አፍሪካ፤ በውቢቷ ባሕር ዳር