የጣና ፎረም ተሳታፊ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ባሕር ዳር ከተማ መግባታቸውን ቀጥለዋል።

17

 

የናይጄሪያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን፣ የአፍሪካ ከፍተኛ መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ታዋቂ የአፍሪካዊ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኞች እና ጥናት እና ምርምር ላይ የሚሳተፉ ምሁራን እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ መሪዎች የጣና ፎረምን ለመሳተፍ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

የፎረሙ ተሳታፊ እንግዶች በባሕር ዳር ደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፎረሙ ላለፉት 11 ዓመታት የተካሄደ ሲኾን ዘንድሮም ለ12ኛ ጊዜ በአፍሪካ ሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየመገጭ መስኖ ፕሮጄክት፤ ከ18 ዓመታት ተስፋ እስከ ተግባር !
Next articleየጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የውኃ ጥም ሊቆረጥ ይኾን?