
በጎንደር እና አካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም በደንቢያ አርሶ አደሮች ቀየ በ2000 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የተጀመረው የመገጭ መስኖ ፕሮጄክት በወቅቱ በነበረው የፕሮጄክት አመራር ድክመት እና የመልካም አሥተዳደር ችግር ምክንያት ለ18 ዓመታት ሳይጠናቀቅ ቆይቶ ነበር።
ይህም በክረምት ጎርፍ ንብረት የሚያጠፋ፣ በበጋ ደግሞ የውኃ ጥም የሚያስከትል ባዶ ተስፋ ኾኖ ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአንድ ወቅት ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳረጋገጡት ይህ ለዓመታት ዘግይቶ የነበረ ፕሮጄክት በተወሰደ ቁርጠኛ አመራር መፍትሔ አግኝቷል።
በዚያም ምክንያት ግንባታውም ቀን ከሌሊት በፈረቃ እንዲፋጠን በመደረጉ እነኾ ለምርቃት በቅቷል።
መገጭ ግድብ በመስኖ ልማት አርሶ አደሮችን ከዝናብ ጠባቂነት ወደ አምራችነት የሚያሸጋግር ከመኾኑም በላይ፣ ለጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ እና ለዓሣ እርባታም አዲስ ዕድል የፈጠረ ነው።
ኢትዮጵያ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ አጠናቅቃ እንደ መገጭ ያሉ ፕሮጄክቶችንም በተግባር ስታረጋግጥ፣ በራሷ አቅም፣ ጊዜ እና ሀብት ታሪኳን መጻፏን እንደማታቆም ግልጽ መልዕክት አስተላልፋለች።
የመገጭ ግድብም የሀገር በቀል አቅም እና የጋራ እድገት ራዕይን ሕያው አድርጓል።
#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ:-ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
