“የመገጭ ግድብ ፕሮጄክት ከተስፋ ወደ ፍሬ”

10

 

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ አቅራቢያ የተገነባው የመገጭ ግድብ ፕሮጄክት በሀገሪቱ ከተያዙት ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው።

ፕሮጄክቱ ሰፊ የእርሻ መሬትን በዘመናዊ የመስኖ እርሻ በማልማት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ፣ የጎንደርን እና አካባቢውን ሕዝብ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር እንደሚፈታ፣ ተጨማሪ የቱሪዝም ሀብት በመኾን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተስፋ ተጥሎበታል።

ከዘመናዊ የመስኖ እርሻ ልማት ባለፈ ለዓሣ ሃብት ልማትም ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም ከዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመኾን ትልቅ ተስፋ ጥለው የግንባታውን መፋጠን በጉጉት ሲጠብቁት ኖረዋል። ተስፋቸው እውን ኾኖ ግንባታው ተጠናቅቆ ማየትን ሲናፍቆት ቆይተዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ቀደም ሲል እንደተናገሩት መገጭ ለጎንደር እና አካባቢው ማኅበረሰብ ትልቅ የልማት ተስፋ ነው። ፕሮጀክቱ ከነበረበት ችግር ወጥቶ ለዚህ ደረጃ መድረሱ ከፍተኛ የመንግሥት ቁርጠኝነት የታየበት መኾኑን ጠቁመዋል።

ግድቡ ለበርካታ ዓመታት ግንባታው ሲጓተት ቢቆይም በቅርቡ በተደረገው የመንግሥት ልዩ ክትትል እና የአሠራር ማሻሻያ ተደርጎለት እና የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ደርሶ ዛሬ ተመርቋል። መገጭ ከተራዘመ የሕዝብ መጠበቅ እና ተስፋ ወደ ተጨባጭ ፍሬ ተቀይሯል።

#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

✍️ ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የመገጭ መስኖ ግድብን መረቁ።
Next articleየመገጭ መስኖ ፕሮጄክት፤ ከ18 ዓመታት ተስፋ እስከ ተግባር !