
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ ሬጅመንት በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ላይ ኾኖ በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ ማኅደረ ማርያም ቀበሌ ለሚገኙ የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን ሰብል የመሠብሠብ ሥራ አከናውኗል።
የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኢንጂነር ሌተናል ኮሎኔል ምሥራቅ መንበር ለአቅመ ደካማ አርሶ አደሮች የተደረገውን ድጋፍ ሠራዊቱ በራሱ ተነሳሽነት እንዳከናወነ ገልጸዋል።
ሠራዊቱ እየሠራ ባለው ሥራ ከሕዝብ የወጣ የሕዝብ ልጅ መኾኑን አሳይቷል ብለዋል።
ሠራዊቱ የሕዝብ አለኝታነቱን በተግባር እያሳየ የሚገኝ መኾኑን ተናግረው በዚህ እገዛ ሠራዊቱ አጠቃላይ ስድስት ሄክታር የሸፈነውን ሰብል ለአቅመ ደካሞች መሠብሠባቸውን አስረድተዋል።
ሰብላቸው የተሠበሠበላቸው አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ሠራዊቱ በአካባቢያቸው በመሰማራቱ ተረጋግተው ወደ ልማት ሥራ መግባታቸውን በመግለጽ ለተደረገላቸው የጉልበት ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል። መረጃው የምስራቅ ዕዝ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
