
የሴራሊዮን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኤርነስት ባይ ኮሮማ የአፍሪካ ከፍተኛ መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ የሚያደርጉትን የጣና ፎረም ውይይት ለመካፈል ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኤርነስት ባይ ኮሮማ ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአፍሪካ ሰላም እና ደኅንነት ላይ የሚመክረው ጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ ከጥቅምት 13/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
አሁን ላይ የጣና ፎረም ተሳታፊ ከፍተኛ የአፍሪካ መሪዎች እና የጉባኤው ተሳታፊ ታዋቂ አፍሪካዊ እንግዶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ወደ ባሕር ዳር ከተማ እየገቡ ይገኛሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
