
በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር እንጅባራ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እያደረገ ላለው ታላቅ ተጋድሎ እና እያስመዘገበ ላለው ድል አጋርነታቸውን ለማሳየት የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
ሰልፈኞቹ የሀገር ጠላት የኾኑት ግብጽ፣ ሻዕቢያ፣ ሕገ ወጡ ሕወሃት እና በጽምዶ ስም የተደራጁ ሀገር አፍራሽ ሴረኞችን በአደባባይ አውግዘዋል።
በኢትዮጵያ ሕዝቦች የተባበረ ክንድ እና በጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መከታነት የሀገራችን ብልጽግና እውን ይኾናልም ነው ያሉት።
መከላከያ ሠራዊቱ እያከናወነ ለሚገኘው ሀገር የማዳን ተልዕኮ ያላቸውን ክብር እና የማይነጥፍ ደጀንነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ስልፈኞቹ ገልጸዋል።
የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ኑርልኝ ሰውነት የሀገር መከላከያ ሠራዊት በጀግንነት ታሪኩ ጸንቶ በየዘመኑ የሚነሱ የውስጥ ባንዳዎችን እና የውጭ ባዳዎችን ሴራ በማምክን ሀገርን አጽንቶ ቆይቷል ብለዋል። አሁንም ይህንን ጀግንነቱን ሀገር ለማፍረስ በተነሱ ጠላቶች ላይ በተግባር አረጋግጧል ነው ያሉት።
መከላከያ ሠራዊቱ እየፈጸመ ለሚገኘው የጀግንነት ተጋድሎ የእንጅባራ ከተማ ሕዝብ አጋርነት እንደማይለየውም ገልጸዋል።
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ እና የንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ በውቀት ገዛኸኝ የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የሀገር አለኝታ እና የሰላማችን ዘብ መኾኑን ተናግረዋል፡:
የኢትዮጵያ የልማት ግስጋሴ እንቅልፍ የነሳቸውን ታሪካዊ ጠላቶችን እና የውስጥ ባንዳዎችን አደብ በማስገዛት ሀገርን በደሙ እያጸና መኾኑንም ነው ያነሱት።
ዘጋቢ:- ሳሙኤል አማረ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
