
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገር ሉዓላዊነት እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት የሚደግፍ፤ የባንዳ እና ባዕዳንን ዕኩይ ተግባር የሚቃወም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በከሚሴ ከተማ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ ነዋሪዎች ለአሚኮ በሰጡት ሀሳብ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የማንደራደርበት ቀይ መስመራችን ነው ብለዋል።
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም የመከላከያ ሠራዊቱ የሕዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ቀን ከሌት እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ለመደገፍ ማኅበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ድጋፉን እያሳየ ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ ሰላም እና ለሀገር ሉዓላዊነት የቆመ ብርቱ ክንድ በመኾኑ የላቀ ክብር እንደሚገባው ገልጸዋል።
ሠራዊቱ ሀገርን ለማፍረስ የሚሠሩ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን ሴራ በማክሸፍ የኢትዮጵያን አሸናፊነት እያበሰረ የሚገኝ ጀግና ሠራዊት መኾኑንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
