
በደብረ ማርቆስ ከተማ የሀገርን ሉዓላዊነት እና የሕዝብን ሰላም ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት የሚደግፍ እና የሀገር አፍራሾችን እኩይ ሴራ የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። በዕለቱ ወደ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ የወጡ የከተማዋ
ነዋሪዎች፣ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ሀገር ለማተራመስ የሚያደርጉትን የጥፋት መንገድ በመቃወም ለሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት እና ደጀንነት አረጋግጠዋል።የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ መልካሙ ሽባባው በድጋፍ ሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት
“ሕዝቡ ጥፋትን እና ትርምስን ፈጽሞ ተቃውሟል፤ የሰላም እና የሕግ መከበር መሻቱን በዓደባባይ ገልጿል” ብለዋል።ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የጸጥታ ኀይሎች እየወሰዱት ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ደኅንነት እና ዘላቂ ሰላምን
ለማረጋገጥ የሚከናወን ሕጋዊ ግዴታ በመኾኑ ኅብረተሰቡ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ያልተቋረጠ ድጋፍ እንዲያደርግም አሳስበዋል።በተጨማሪም የሀገርን ህልውና እና የሕግ የበላይነት ለማስከበር በየግንባሩ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙ የሕዝብ እና የሀገር አለኝታ ለኾኑ የጸጥታ ኀይሎች
ምሥጋና እና አክብሮት አቅርበዋል።የሀገር አንድነት እና ሰላም የሚጸናው በሕግ የበላይነት፣ በሕዝብ እና በጸጥታ ኀይሎች መካከል በሚኖር ጠንካራ ትብብር መኾኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
